ካናቢስ እና የአዕምሮ ጤና
አንድ ሰው ካናቢስ የመጠቀም ችግር አለበት ከሚያስብሉ ባህርያት(ምንጭ DSM-5 TR) :-
✅አጠቃቀማቸውን ለመመጠን መቸገር (ለረጅም ሰአት መጠቀም: ካሰቡት ልክ በላይ መጠቀም፤ መጠኑን ለመቀነስ ወይንም ለማቆም እየፈለጉ አለመቻል ፤ አምጡ የሚል ውስዋስ
✅ በማህበራዊ ህይወት፣ በስራ: በቤተሰብ ጉዳዮችን ላይ ችግር ካስከተለ
✅ በአደገኛ ሁኔታዎች እና ወቅቶችም መጠቀምን መቀጠል( ጡዞ ማሽከርከር፤ የጤና እክል አስከትሎም መጠቀሙ ከቀጠለ)
✅ ለማቆም ሲሞክሩ የስሜትና አካላዊ ጤንነት መዛባት/Withdrawal( መነጫነጭ፣ መጨናነቅና መቅበጥበጥ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድብርት) እና በጊዜ ሂደት የሚፈልጉትን ስሜት ለማግኘት የሱሱን መጠን መጨመር ካስፈለገ
*
▶️ ካናቢስና ተጓዳኝ የአእምሮ ህመሞች
🔹 ካናቢስ ከሳይኮሲስ (ከእውነታው ማፈንገጥ/ ጥርጣሬ: እንግዳ የሆነ ድምጽ መስማት: ለሌሎች የማይታዩ ነገሮችን ማየትና የመሳሰሉ)፣ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት ጋር ይያያዛል::
*
▶️ ካናቢስ ለ ስኪዞፍሬንያ(ከባድ የሳይኮሲስ ህመም) ያጋጣል?
🔹በዴንማርክ በተሰራ ጥናት መሰረት:
▫️በተለይም ወጣት ወንዶች የካናቢስ ተጠቃሚዎች፣ በተለይም ከ 16-25 አመት ያሉት ላይ የ ስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ጨምሮ ታይቷል:: በጥናቱ እንደተመላከተው የካናቢስ ተጠቃሚነትን መቀነስ ቢቻል 1/5 ኛ ያህል ስኪዞፍሬኒያን ማስቀረት ይቻል ነበር:: (Hjorthøj C, Compton W, Starzer M, et al. )
🔹 በ ስዊድን ለ15 አመታት ካናቢስ የሚጠቀሙ ሰዎችን በመከታተል በተሰራ ጥናት ከ50 ጊዜ በላይ የተጠቀሙ ሰዎች በ6 እጥፍ ተጋላጭነታቸው ጨምሯል::
🔹በተለይም ከአፍላ እድሜያቸው ጀምረው ረዘም ላለ ጊዜ የተጠቀሙ ሰዎች ለ ስኪዞፍሬኒያ ተጋላጭነታቸው ይጨምራል:: በዚህ እድሜ የአእምሮ ህዋሳት የሚጎመሩበት እድሜ ነውና ሱሱ በዚህ ሂደት ላይ ተጽዕኖ ስለማያሳድር ነው::
🔻 እንደምክንያት የሚነሱ ነጥቦች:-
▪️ የዶፓሚን ንጥረነገር መዛባትና የአእምሮን ስራ በማወክ
▪️ከሌሎች ስነህይወታዊ እና ዘረመሌዛዊ ጉዳዮች ጋር በጋራ አጋላጭነት መጨመር(Stress- vulnerability model)
ሱስ ለማቆም የሚረዱ ነጥቦች
🖊 እስካሁን እንዳታቆሙ ሰበብ የሆኑባችሁን ነገሮች ከዚህ መረጃ ጋር አመዛዝኗቸውና ራሳችሁን ጠይቁ::
🖊 የማቆም ሂደቱን የምትጠቀሙትን መጠን በመቀነስ መጀመር ይቻላል::
🖊ዶፓሚናችሁ በሌሎች ነገሮች እንዲመነጭ በማድረግ(በስፖርት: በንባብ: ፊልም በማየት: ከከተማ ወጣ ብሎ በመዝናናትና ወዘተ) የካናቢሱን አስፈላጊነት ቀስ በቀስ መግታት ይቻላል::
🖊 በጊዜ ሂደት ካናቢሱን በመሞከር ተጀምሮ ከተለያዩ ነገሮች ጋር በማስተሳሰር መጠቀሙን እንደገፋችሁበት: በጊዜ ሂደት ማቆም የመጠቀም ዑደቱን ያስቀጠሉ (ደስታን መሻት/reinforcement፣ ወይንም ሲያቆሙ ጊዜ የሚፈጠሩ ደባሪ ስሜቶችን/Withdrawal symptoms ላለማስተናገድ) በመግታት ባህርይውን ማረቅ ይቻላል:: በ learning theory መሰረት ማለት ነው!
🖊 ከባለሞያ ጋር መመካከር እና የባለሞያ እርዳታ ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው።
Healthy life rehabilitation center
(ኸልዚ ላይፍ የሱስ እና የአዕምሮ ተሀድሶ ህክምና ማዕከል )
"The place where recovery starts"
ጤናማአዕምሮጤናማ_ህይወት!!!”
✅Contact Us
@Healthyliferehab
@Healthyliferehab
For appointment
📞0967666667
📞0962333334
📞0936196148
