You are currently viewing የሱስ ምልክቶች ምንድናቸው?

የሱስ ምልክቶች ምንድናቸው?

የሱስ ምልክቶች ምንድናቸው?
  ከላይ እንደተጠቀሰው አንድ ሰው አንድን ንጥረ ነገር (Substance) ለረጅም ጊዜ በተደጋጋሚ ሲጠቀም እና በዛ ንጥረ ነገር ላይ በአካል፣ በባህርይ እና በስነልቦና ጥገኛ ሲሆን ሱሰኛ ይባላል። እሱ ራሱ ድርጊቱንና ውሳኔውን ከሚቆጣጠረው በላይ ሱሱ አዕምሮውን ስለሚቆጣጠረው ለማቆም ቢፈልግ እንኳን እጅግ ከባድ ይሆንበታል። ሱስ ያለበት ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች እንደሚጠቀመው ነገር ሊለያዩ ቢችሉም ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ግን የሚከተሉትን ይመስላሉ። 
👉ሱሱን ለመጠቀም (ለማስታገስ) ከፍተኛ ጊዜ ማጥፋት
👉ለማቆም ወይም ለመቀነስ መቸገር
👉አምጣ አምጣ የማለት ስሜት
👉ለማቆም ወይም ለመቀነስ በሚሞክርበት ጊዜ የተለያዩ አካላዊ የሆኑ የሕመም ምልክቶችን ማሳየት
👉የንጥረ ነገሩን መጠን በየጊዜው መጨመር
👉የአካል እና የአዕምሮ ጤና መቃወስ እንደሚያስከትል እያወቁ መጠቀም
👉የስራ እና የትምህርት መስተጓጎል
ሃላፊነቶችን አለመወጣትና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ መግባት
👉ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ እና ከስራ ባልደረባ ጋር ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት ውስጥ መግባት
👉ንጥረ ነገሮቹን ተጠቅሞ ሕይወትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ድርጊቶችን ማከናወን። ለምሳሌ:- መኪና መንዳት

ከሱስ መላቀቅ  ይቻላል?
  አዎ ይቻላል! ማንኛውም አይነት ሱስ ያለበት ሰው ተገቢው የስነአዕምሮ ሕክምና ክትትል ከተደረገለት ሙሉ በሙሉ ማገገም እና መላቀቅ ይችላል። ሆኖም ግን ከሚያደርገው የሕክምና ክትትል በላይ የራሱ ዝግጁነት እና ቁርጠኝነት እጅግ አስፈላጊ ነው። 
🖊 ከሱስ ለመላቀቅ ከሚደረገው የስነአዕምሮ ሕክምና በዋነኝነት የሚሰጠው የንግግር ሕክምና (Psychotherapy) ነው። ይህም አንድ ሱሰኛ ሰው ከሱሱ ለማገገም በሚያደርገው ጉዞ በእጅጉ ያግዘዋል።

🖊ከዚህ በተጨማሪም አንድ ሰው የአንድ ንጥረ ነገር ሱሰኛ (ጥገኛ)ሲሆን ሰውነቱ በከፍተኛ ሁኔታ ይህን ንጥረ ነገር ስለሚላመደው ለማቆም ወይም ለመቀነስ በሚሞክርበት ጊዜ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች (Withdrawal Symptoms) ሊያሳይ ይችላል። ለምሳሌ አንድ የአልኮል ሱስ ያለበት ሰው ሰውነቱ የለመደውን መጠን ያህል አልኮል ካላገኘ የመንቀጥቀጥ፣ የመቃዠት፣ ለሌሎች የማይታዩ/ የማይሰሙ ነገሮችን ማየት/መስማት እና የመሳሰሉ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል።
🖊ስለዚህም ከንግግር ሕክምናው (Psychotherapy) በተጨማሪ እነዚህን ምልክቶች በመድሃኒት ማከም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ከነዚህም በተጨማሪ ለሱስ የሚጋብዙ ሁኔታዎችን ለይቶ ማወቅ እና ከእነሱም መራቅ የማገገም ሒደቱን ሊያግዝ ብሎም ከሱሱ ከወጡ በኋላ እንዳያገረሽ ሊከላል ይችላል። 
 የህክምና አገልግሎት ለማግኘት
👇👇👇
   Healthy life rehabilitation center

(ኸልዚ ላይፍ የሱስ እና የአዕምሮ ተሀድሶ ህክምና ማዕከል )
   “The place where recovery starts”

አድራሻ 👉 ከልኳንዳ ወደ ፍሪዶሮ በሚወስደው መንገድ አሚን ብሎኬት ማምረቻ 100 ሜትር ገባ ብሎ

“የአዕምሮ ጤንነትዎ ያሳስበናል!!!
ጤናማ አዕምሮ ጤናማ ህይወት!!!”

✅ Contact us
@Healthyliferehab
@Healthyliferehab

Contact Us
📞0967666667
📞0962333334
📞0936196148

Leave a Reply